nazret.com
 

Archives for: September 2005

09/30/05

Permalink 05:05:01 pm, by nazret.com, 0 words, 797 views   English (US)
Categories: News

Abraham Yayeh


አብርሃም ያየህ የመለስ ፕሮፖጋንዲስት ሆኑ
በአውሮፓና በካናዳ ከሚያካሂዱት የፀረ-ቅንጅትና ፀረ-ኅብረት ቅስቀሳ በላይ ባለፈው እሁድ አንድ ኢትዮጵያ በተባለ አፍቃሪ ወያኔ ራዲዮ መግለጫ የሰጡት አብርሃም ያየህ መለስ በሥልጣን ላይ ካልቆዩ የትግራይ ሕዝብ የሕይወት ዋስትና እንደማይኖረው፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራር ብቃት እንደሌለውና እንዲያውም የትግራይ ሕዝብ እንደሚጠላቸው ገለጡ።

በደርግ የመጨረሻ ዓመታት ስለ ወያኔ የጐሠኝነት አቋምና አጣፊ አጀንዳዎቹ በሰፊው በማስረዳትና ሕዝቡን በመቀስቀስ የታወቁት አቶ አብርሃም ያየህ ጐራ በመለወጥ በአሁኑ ሰዓት ስለ መለስ ዜናዊ ስብዕናና ስለ ድርጅታቸው ታላቅነት በሰፊው በመተንተን የፕሮፖጋንዳው ዋና ተዋናይ ሆነዋል።

አቶ አብርሃም ያየህ ከደርግ ውድቀት ማግሥት ጀምሮ በየአገሩ እየተዘዋወሩ በግል ስለ መለስ ዜናዊና ባጠቃላይም በወያኔ/ኢሕአዴግ ከፋፋይ አጀንዳ ላይ በውጭ በሚገኙ ራዲዮ ጣቢያዎች ሰፋፊ መግለጫዎች በመስጠት፣ በጋዜጦችም ላይ እንዲሁ የማያልቅ ሐተታዎች በማቅረብ የቆዩ ናቸው። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ያነጣጠረ የዘመቻ ግንባር ከፍተዋል።

የአቶ አብርሃም ያየህ የኅብረቱ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አረጋዊ በርሄን፣ በሕክምናና በኢትዮጵያዊነት የሚታወቁትን ዶክተር አስፋ ነጋሽን፣ ፕሮፌሰር ጣልሁ ይልማን የፕሮፖጋንዳቸው የጥቃት ዒላማ አድርገዋቸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ቅንጅቱንና ኅብረቱን የትግራይ ሕዝብ እንደሚጠላቸውና ከክልሉ እንዳባረራቸው ተናግረዋል። ስለሆነም የትግራይ ህዝብ እውነተኛ ተወካይ ወያኔ፣ መለስ ዜናዊም የኅብረተሰቡ አዳኝ መሆናቸውን ለማብራራት ሞክረዋል። «መለስ ዜናዊ በዩ ኤ ሥራ ሊያገኝ የሚችል ምሁር ነው። የሚቀርቡት የትግራይ ሕዝብ ነው» ብለዋል።

ግለሰቡ ከአንድ ሰዓት በላይ ለወያኔ ተቀጥላ በሆነው ራዲዮ የወያኔን ተፈላጊነት፣ ለትግራይ ሕዝብ መኖር ዋስትናነት፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች መለስን ለመተካት አለመቻልና በተዘዋዋሪም ወያኔ ለማንም በምንም ሰዓት ሥልጣን ሊለቅ እንደማይችል ያላቸውን እምነት ገልጠዋል።

ከልሳነ ሕዝብ መስከረም 20 ቀን 1998

PermalinkPermalink 2 comments
Comment continues below ↓
Google
 
Web www.nazret.com

advertisement

Permalink 01:53:48 pm, by nazret.com, 63 words, 219 views   English (US)
Categories: News

Ethiopian opposition cancels rally, blames govt

Ethiopian opposition cancels rally, blames govt

By Tsegaye Tadesse

ADDIS ABABA (Reuters) - Ethiopia's two main opposition parties on Thursday said the government forced them to call off post-election protest rallies planned for the weekend, in violation of their constitutional rights.

Read the article and post your comments.

Please limit your comments specific to the topic.

Sign up to post your own discussion topic

PermalinkPermalink 132 comments
Comment continues below ↓
Google
 
Web www.nazret.com

advertisement

Permalink 06:04:33, by

An unexpected error has occured!

If this error persits, please report it to the administrator.

Go back to home page

Additional information about this error:

Requested User does not exist!