በኮሎመበስ ኦሀዮ የደበረ ሰላም ቀዱስ ገብርኤል ምዕመናን በሙሉ

November 18th, 2008

በኮሎመበስ ኦሀዮ የደበረ ሰላም ቀዱስ ገብርኤል ምዕመናን በሙሉ
በቤተ ክርስቲያኑ የተከሰተዉን ችግር ለመፍታት ጉዳዩ ያሳሰበን የተወሰኑ የሰበካ ጉባኤ አባላትና ምዕመናን በፍቃድ ከተሰባሰቡና በሽመግልና ከሚረዱ የቤተክርስቲያኑ አዛዉንቶች ጋር በመሆን ተገቢዉን ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን። እስካሁን ባለዉ እንቅስቃሴ በተለየዩ ግልጽነት በጎደላቸዉ ሁኔታዎቸ ሳቢያ ጥረቱ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ወደአልተጠበቀ ጎዳና በማምራት ላይ ነዉ። የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን አባታዊ የሆነና ወቅታዊ መፍትሄ ለመስጠት ፍቃደኛ ሆነዉ አልተገኙም። በምእመናን ፊት ይቅር ለእግዚአብሔር ተባብሎ ሠላም ከማስፈን ይልቅ፣ ግላዊና ቡድናዊ ስሜት እንዲሰፍን እየተደረገ ነዉ። ችግሩ ከአቅም በላይ ሆኖ በመገኘቱ የተወሰንን የሰበካ ጉባኤ አባላት በግልና በጋራ በመሆን፤
2.
በአደባባይ ከደረሰብንን መረጃ አልባ ከሆነ ዉንጀላና ዘለፋ ስማችንን ለማንጻት፣
ይህ እርምጃ ለኛም ሆነ ለጠቅላላዉ ምእመናን አሳዛኝ ስሜት እነደሚያሳድር ይታወቃል። ይሁን እንጂ ቀና መንፈሱ ካለ በጋራ ጉዳዩን ለማስተካከል እድሉ አሁንም በእጃችን ላይ ነዉ።እንደሚታወሰዉ ባለፈዉ ወር መጀመሪያ ላይ ሀይማኖታችንንና የመከባበር ባሕላችንን ባልተጠበቀ ሁኔታ የገብርኤል ታቦት ባረፈበት የተቀደሰ ቦታ ላይ ተቆሞ ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና አንዳንድ አባላት ይሰነዘር የነበረዉ ዝቅ ያለ ቃላት፣ የለቱን ምዕመናን አንገት የአስደፋ የሐዘን ቀን ሆኗል። በእለቱ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ “አስቀድመዉ አላሰወቁኝም” ያሉትንና በተወሰኑ የሰበካና የህንፃ ኮሚቴ አባላት አማከይነት ለምዕመናን የታደለዉን የቤተ ክርስቲያኑን ወጪና ገቢ፣ ችግርና መፍትሄ በከፊልም ቢሆን የጠቆመዉ ሪፖርት ለተቀደሰዉ ስፍራ መናጋት ምክንያት ሆኗል። በመሰረቱ ሪፖርቱ በዚያ ሁኔታ መታደል በራሱ የነበረዉን የዉስጥ አሰራር ችግር የሚያመለክትና የተለያዩ ጥያቄዎች እንዲነሱ የሚጋብዝ ነበር። ነባሮቹ የሰበካ ጉባኤ አባላት የሚወርዱበትን ምክንያት በግልጽ አሳዉቆ ፣ በእጃቸዉ ሚገኘዉን ንብረትና ገንዘብ አወራርደዉ ላደረገት አፍራሽም ሆነ ገንቢ አስተዋጽኦ ወቀሳም ሆነ ምስጋና ከምእመናን ተሰጥቶ ወደሚቀጥለዉ እርምጃ መጓዝ የእለቱ አላማችን ነበር። ይህ ሊሆን አልቻለም። በተድበሰበሰና በአቋራጭ የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር በተለይም የፋይናንስ አቋሙን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአስተዳዳሪዉ ሙሉ ቁጥጥር ስር ለማድረግ የተጀመረዉ እርምጃ በመተጓጎሉ መላዉ ምዕመናን እደሚያስታዉስቱ ከፍተኛ ቁጣ ሊያስነሳ በቀቷል። አስተዳዳሪዉ በሃይማኖት መሪነት እና የአባትነት ባህርይ፣ በትእግስት ሁኔታዉን በማስረዳትና ለቀረበዉ ሪፖርት መልስ በቃል ወይም በሌላ ቀጠሮ በተመሳሳይ ሪፖርት እንዲሰጥ በማድረግ ምዕመናኑን አረጋግቶ ቤተ ክርስቲያኑ ሳይናጋ የሚጓዙበትን ሁኔታ ሊፈጠሩ በተገባ ነበር። ከዚህ ይልቅ የተወሰኑ ሰበካ ጉባኤ አባላትን በገንዘብ ዘራፊነት፣ በግል ጥቅም አሳዳጅነትና በግል ህይወት ጭምር ጣልቃ በመግባት ሲኮነኑ ተደምጧል። የድምፅ ማጉያዉን በመቀበል ለምዕመናኑ ሁኔታዉን ገልጾ ለማረጋጋት የሞከሩትን ግለሰቦች እድሉን ከመስጠት ይልቅ ለድበዳባ እንደተጋበዙ ተደርገዉ ሲወነጀሉ ተሰምቷል። በማሳረጊያዉም ወቅት አሜን ከመባሉ በፊት የተጀመረዉ ስድብ ሳይረጋጋና የተለመደዉ የመሰናበቻ ቡራኬ ሳይደረግ በቁጣ ወደ መቅደሱ በመግባታቸዉ ምዕመናኑ ግራ በተጋባና በሀዘን ስሜት ከጠረጴዛቸዉ የተደረደረዉን ጸበል እየተቃመሱ እንዲበተን ሆኗል።
በእጃችን የሚገኘዉን ንበረትና ገንዘብ ህጋዊ ባልሆነ መነግድ ለመዉሰድ እየተደረገ ያለዉን ሙከራ ለማቆምና ይሕንኑ ንብረትና ገንዘብ ሕጋዊ በሆነ መልኩ ባለቤት ለሆነዉ የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ለመረካከብ ሲባል ጉዳዩን ወደ ሕግ ፊት እንድንወሰድ ተገደናል።
2
በዚህች በተቀደሰች ቦታ እንዲሁም ነፃነት በሰፈነባትና ከአንገታችን ቀና ብለን በምንራመድበትና በምንተነፍስበት አሜሪካ አገር፤ ያን መሰል ነፃነት የሌለበት፣ ሕግን ያልተከተለ አሳዛኝ ሁኔታ ማስተዋሉ የሚያስገርም ነበር። አስተዳዳሪዉ በኢትዮጵያና በአሜሪካ ባሉ ምዕመናን ያለዉን ልዩነትና አንድነት፣ የኑሮዉ ዉጣ ዉረድ ፣ መብትና ግዴታ በቅጡ ሰለመገንዘባቸዉም ጥያቄ ዉስጥ ያገባን ጉዳይ ነበር። በተከታታዩ ሳምንታት ይህንን ችግር መላዉ ምዕመናን በተገኙበት ለመፍታት ጥረት ቢደረግም፣ በግልጽ የተስተዋለዉ ጉዳይ ግን ቤተክርስቲያኑን በጥቂቶች ቁጥጥር ስር ለማዋል የተያዘዉን እንቅስቃሴ ነበር። ምዕመናኑ በልተገናዘበዉና በልተወከለበት ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኑ ሀብትና ንብረት በአጠቃላይ ህልዉናዉ በአስተዳዳሪዉ እጅ ብቻ እንዲዉልና፣ ደረጃ በደረጃም ከአባላቱ ዉጭ በሆነ አካል እንዲዛወር እርምጃዉ ተይዟል። መስራች አባለቱ እንደምናስታዉሰዉ፤ ቤተ ክርስቲአኑ ሲቋቋም በአሁኑ አስተዳዳሪ አንደበት የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አቋሙ ገለልተኛና የማንንም ስም ሳይጠራ የቅዳሴዉ ሥነ ሥርዓት እንደሚያካሔድ ነበር። የደበሩን ታቦት ባርኮ ለማስጋበት ጳጳስ ስለሚያስፈልግ በእለቱ ሥነ ሥርዓት በሚከተሉተ ሲኖዶስ መሰረት የጳጳስ ስም ቢጠቀስ ግራ እንዳየጋባ ምእመናን ሁሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዉ ነበር። ከጥቂት ወራት ወዲህ ለምዕመናኑና ለሰበካ ጉባኤዉ አባላት ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ በቀዳሴዉ ሥነ ሥርዓት መሀል የጳጳስ ስም እየተጠቀሰ ሲቀደስ እያዳመጥን ነዉ። አንዳንድ አባላት የቃላቸዉን ማፍረስ መንስዔዉን ጠይቀዋቸዉ መልሳቸዉ “ምዕመናኑ እኛ እነደምንመራቸዉ ነዉ” ብለዋል። አቅጣጫዉ ያሳሰባቸዉና ቤተክርስቲያኑ ከምዕመናኑ እጅ ዉጭ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የተገነዘቡ አባላት ለቀዉ እንዲሄዱም ምክንያት ሆኗል። በርካታዎቻችን ጉዳዩን በዉይይት መፍታት ይቻላል በማለት ሁኔታዎችን እየተጠባበቅን ነበር። ይሁን እንጂ የቀጠለዉ ሁኔታ ችግሩን የሚያሰፋ እንጂ የሚያጠብ ሆኖ አልተገኘም። ቀደም ሲል ለምዕመናኑ በታደለዉ ሪፖርት እንደተጠቆመዉ በዘተፈቀደ አለምንም ኦዲተር በቤተ ክርስቲያኑ ስም እየወጣ ያለዉ ገንዘብ ከገቢዉ ጋር ጨርሶ ሊመጣጠን አልቻለምና መፍትሔ በአስቸኳይ እንሻለት ነበር። ይህ አካሄድ ያሳሰባቸዉ አንዳንድ የሰበካ ጉባኤ አባላትና ምዕመናን አንድ መፍትሄ እስኪደረስ ድረስ ቢያንስ የአባላቱ ዋና አላማ ለሆነዉ የቤተ ክርስቲያኑ ህንጻ ማሰሪያ የማይንቀሳቀስ ገንዘብ በባንክ መክፈት አስፈላጊ መሆኑን በመጎትጎት የህንፃ ኮሚቴ እንዲመሰረት ተደርገ። ይኸዉ ኮሜቴ በሁለት አመት ዉስጥ እቁብ በማሰባሰብ $10,000.00 ብር፣ መኪና ሎተሪ በመጣል $12,000.00 ብር፣ እንዲሁም የተቀረዉን ከምዕመናን በማሰባሰብ በጠቅላላዉ $42,000.00 ብር ገቢ ሊደረግ በቅቷል። ገንዘቡ በምን መልክ እንደሚቀመጥ በተደረገዉ ዉይይት፣ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ “እኔ አስተዳደር አልቻልኩም እናንተ አስተዳድሩት እኔ ሀይማኖቱን እየዛለሁ” በማለት በሰጡት ቃል መሰረት ሰበካ ጉባኤዉ ከሕንፃ ከሚቴ ጋር ተባብሮ በቤተ ክርስቲያኑ ስም የባንክ አካዉንት ከፍቶ ገንዘቡ እንዲቀመጥ አድርጓል። ይህ እርምጃ ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ምረቃና ምስጋና ሊያሰጠዉ ሲገባ ተቃራኒዉ ተከስቶ አብዛኛዉን የሰበካ ጉባኤ አባላት ግራ ሲአጋበዉ ሰንብቷል። ገንዘቡን ዋስትና ባለዉ ሁኔታ ለማስቀመጥ ባደረግነዉ በዚህ እንቅስቃሴ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ቃላቸዉን በመለወጥ “የኔም ስም የሕንፃ ኮሚቴ ባንክ ዉስጥ መግባት አለበት” በማለትና የሰበካ ጉባኤ አባላትን በማስጨንቀዉ ስማቸዉ እንዲታከል ተደርጓል። በዚህ ማህከል በተለያዩ ምክንያቶች መተማመን ባለመፈጠሩ የሰበካ ጉባኤ አባላት ምክክር በማድረግ ከህንፃ ኮሚቴ አንድ፣ ከሰበካ ጉባኤ አባላት አንድ ሰዉ መድቦ ገንዘቡን በሌላ አካዉንት በቤተ ክርስቲያኑ ስም በማዛወር በመጀመሪያ በመኒ ማርኬት በኃላ በሲዲ እንዲታሰር ተደርጓል። ይሁን እንጂ ፣ እርምጃዉ ለሕንፃዉ ገንዘብ እረፍት ሊያሰጥ አልቻለም።
3
ቄስ ያሬድ ገ/መድኅን በመንፈሳዊ አባትነታቸዉ ለምዕመናን ትምህርት እየሰጡ አስተዳደሩን ለተመረጡ የሰበካ ጉባኤ አባላቶችና ለሌሎች ኮሚቴዎች መስጠት ለምን እንድአስጨነቃቸዉ ግራ ያጋበንን ጥያቄ በጉልህ እያስተዋልነዉ ነው። ከላይ እንደጠቆምነዉ ለሕንፃ ማሰሪያ የተቀመጠዉን ገንዘብ አስተዳዳሪዉ በጃቸዉ ለመቆጣጠር ወደባንክ በመሄድ “ እነኝህን አባላት አላቀቸዉም፣ የቤተ ክርስቲያኑን ገንዘብ ሊሰርቁ ነዉ” በማለት አለአግባብ ገንዘቡን ሊያንቀሳቀሱ ሲሞክሩ ተደርሶበት በህግና በጠበቃ ተይዞ ገንዘቡ ላልተወሰነ ግዜ እቀባ ተደርጎበት እንዲቆይ ሆኗል። በሌላ በኩል እንደሚታወሰዉ የሰበካ ጉባኤ አባላት የመጨረሻ ሪፖርት ስናቀርብና ሂሳብ ስንዘጋ ቤተ ክርስቲያኑ የአለበትን የመጨረሻ ወጪዎች የቤት ኪራይና ያየር መንገድ ወጪ ክፍያ ቼክ ተጽፎ ነበር፣ ይሁን እንጂ በዚህም በኩል አስተዳዳሪዉ የአለምንም ኮሚቴ አባል ተሳትፎ ባንኩን ዘግተዉ በማዘወራቸዉ ቼኮች ባዉንስ ሊያደርጉ ችለዋል። ከሁሉም የሚያስገርመዉ ችግሩን በሽምግልና ለመፍታት ደፋ ቀና በማለት በለንበት ወቅት ይህ የባንክ ዉጣ ዉረድ የባሰ ህጋዊ መከራ ዉስጥ ከቶን የረሳችንን ጠበቃ ሊያሲዘን ችሏል። ከዚህ በፊት አሰተዳዳሪዉ ቄስ ያሬድ ገ/መድኅን ታቦቱ ፊት “የእኔ እጄ ገንዘብ ዉስጥ አይገባም ” ብለዉ ቢሉም፣ ይህ ሲፈርስ አይተናል። በመሰረቱ ይህ አሳዛኝ ድርጊት ሲሆን በዚህ በአሜሪካ ለምንገኝ ምዕመናን አዲስ አይደለም። ጥቂት የቤተ ክርስቲያናት በአስተዳደር ጉድለትና በገንዘብ መባከን ምክንያተ ሲፈርሱና ሲከፋፈሉ አይተናል። ይህ በእኛ ቤተ ክርስቲያን ይሆናል ብለን አልጠበቅንም ነበር። ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን መሰረታዊ ችግር ግልጽ ነዉ። ምዕመናኑ በነፃ መድረክ ተዋይቶበት ያፀደቀዉ መተዳደሪያ ደንብ አለመኖሩ ነዉ። በዉስጥ አሰረሩ የመከባበርና የመተማመን በኅል በተለይም ለአስተዳዳሪዉ ሁሉንም አላፊነት የመጣል ሁኔታ አለደንብና ስርዓት መቀጠሉ ነዉ። አስተዳዳሪወ በሚሰጡት መንፋሳዊ ትምህርት ያከበራቸዉ ምዕመናን ብዙ ሊጋፋቸዉ አልወደደም፤ ምክንያቱም መምህር በመሆናቸዉ ስህተትን ማረም ይችላሉ የሚል ዕምነት ስለነበረ፤ ከዓባላቱ መካክል አንዳንዶቹ ለአስተዳዳሪዉ የሰጡት ሙሉ እምነት ገደብ የለሽ ነበር ቢባል ማጋንን አይሆንም። የዉስጡ ችግር ይፋ በወጣበት እለት በአደባባይ በዘራፊነት፣ በግል ጥቅም አሳዳጂነት ከተዳረጉት ማሕከል ጥቂቶቹ አስተዳዳሪዊዉ ዛሬ የሚገለገሉበትን የግል ተሽከርካሪ መኪና ገዝቶ ከመስጠት ጀምሮ፣ በአሜሪካ የጀመሩትን አዲስ ኑሮ ለማቋቋም ከፍተና የገንዘብና የማቴሪያል እነዲሁም የህክምና ድጋፍ ያደረጉ በለዉለታዎች ናቸዉ። ለቤተ ክርስቲያኑ መቋቋምና ማደግም ያደረጉት የጉልበት፣ የገንዘብና የንብረት አስተዋጽኦ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። የተቀረነዉም ለዚህ ቤተ ክርስቲያን መቆም ገደብ የለሽ የሞያና የገንዘብ የጉልበት አገልግሎት በመስጠት የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከዚህ እንዲደርስ ተደርጓል። በዚህ ያልተቆጠበ እንቅስቃሲያችን ሰዎች ነንና ስህተቶች ልናደርግ እንችላለን። ይህ ስህተት ግን ሆን ተብሎ፣ ሌላ አላማ በስተጀርባ ተይዞ የተደረገ አለመሆኑ ግልጽ ነዉ። የደከምንበትን ቤተ ክርስቲያን ዘረፋችሁ፣ ለግል ጥቅማችሁ አደረጋችሁ፣ ለተባልንበት ዉንጀላ ከገለገልነዉ ቅዱስ ገብርኤል በስተቀር ምስክር የለንም። ይህ ቃላችን እውነት ነዉ። አሁንም የደብሩ ምእመናን እዲገነዘቡልን የምንለምናቸዉ ጉዳዮች እነደሚከተሉት እናቀርባለን፦
1. ለህንፃ ማሰሪያ እንዲሆን ተብሎ የተሰበሰበዉን $42,000.00 ቀድሞ ከነበረዉ አካዉንት የቤተ ክርስቲያኑ አሰተዳዳሪ አለአግባብ የሰበካ ጉባኤ አባል የልሆኑትን አቶ ቤካና አቶ ደረጀን ይዘዉ የኮሚቴ አባል እንደሆኑ በማድረግ ከነበረበት አካዉንት አዉጥተዉ ገንዘቡን በአዲስ አካዉንት ሲያስገቡ ይህ ጉዳይ አለአግባብ መደረጉን ባንከ ተረድቶ በባንኩ ጠበቃ ተይዞ በመጣራት ላይ ሲገኝ፤ ገንዘቡም በቀድሞዉ ገንዘብ ያዥ አማካይነት ፍሪዝ እንዲሆን ተደርጓል።
4
2. የቤተ ክርስቲያኑ መተዳዳሪያ አካዉንት $7876.01 ሲኖረዉ አስተዳዳሪዉ የህንንም አካዉንት ዘግተዉ ያለምንም ኮሚቴ አባል አዲስ አካዉንት ክፍተዉ አስገብተዋል።
3.
ይህንን ችግር ለማቃለልና እራሳችንንም በሕግ ዘንድ ነፃ ለማዉጣት
በመኪናው ሎተሪ እድለኛ የሆኑ ጥቁር አሜሪካዊ በህጋዊ መንገድ ለተረከቡት መኪና ታይትል ካሉበት ስቴት(ቴክሳስ) እንዲላክላቸው አስተዳዳሪውን በተደጋጋሚ ጠይቀው እስካዛሬ አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘታቸው ቤተክርስቲያኑን እንደከሰሱ አሳውቀውናል፤ይህ አሳዛኝ ተግባር ከኛ ከክርስቲያን ወገኖች የሚጠበቅ ባላመሆኑ አስተዳዳሪው አስቸኳይ እርማት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
1. የኦሀዮ እስቴት ኦዲተር መጥቶ የቤተ ክርስቲያኑን ወጪና ገቢ እንዲያጣራ
2. በግለሰብ ደረጃ ያለምንም ማስረጃ በአደባባይ ለደረሰብን ዉንጀላ ጉዳዩ በሕግ ጠበቃ እንዲታይ
3. በባንኩ ላይ ስለተፈጠረዉ አላአግባብ የገንዘብ ዝዉርዉር በባንኩና በራሳችን ጠበቆች ተይዞ እንዲጣራ እየተደረገ ነዉ።
መድረክ አግኝተን ከምእመናኑ ጋር በሰላምና በመንሳዊ ፍቅር ለመወያየት እድሉን ለማግኘት ባለመቻላችን እጅግ እናዝናለን። ጉዳዩ ከማናቸዉም በላይ የመላዉ ምዕመናን በመሆኑ፣ መፍትሄ ተገኝቶ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የሚገለገሉበትና የሚያገለግሉበት የተቀደሰ ቦታ እንደሚሆን ተስፋችን ነዉ። በንጹህ ልብ በአገለገልንበትንና በተገለገልንበትን ቤተ ክርስቲያን ስም የቱንም ያህል ብንሰደብም፣ ብንዋረድም፣ ብንዘለፍም፣ አለቅሬታ ለልባችን እርካታ፣ ለመንፈሳችን ኩራት በመስጠት እዉነቱን ለምዕመናኑና ከሁሉም በላይ ለቅዱስ ገብርኤል ትተናል።
የደብረ ሰላም የቅዱስ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ አባላት
ምክትል ሊቀመንበር፦ ዶር፡ እስክንድር ጌታቸዉ
ሂሳብ ሹም ፦ አቶ፡ አንተነህ ከበደ
ሒሳብ ተቆጣጣሪ፦ አቶ፡ በላቸዉ ክንዴ ረታ
ገንዘብ ቤት፦ ወ/ሮ፡ ሂሩት መንገሻ

ይድረስ በኮሎምበስ-ኦሃዮ ለምትገኙ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ&#4

November 18th, 2008

ይድረስ በኮሎምበስ-ኦሃዮ ለምትገኙ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን
ሁላችሁም እንደምታውቁት ዛሬ በኮለምበስ - ኦሃዮ ሶስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ተቋቁመው ለምዕመናን አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው። መድሃኒአለም፤ ሥላሴዎች እንዲሁም አዲሱ ቅዱስ ገብርኤል ናቸው።
በመሰረቱ በኮሎምበስ ነዋሪ እንደሆነ ለሚገመተውና ከ15 ሺህ ላላነሰ ኢትዮዺያዊ ሶስት ቤተክርስቲያን በዛበት የሚያሰኝ ኣይሆንም። አንዱ ሌላውን እንደሚያዳክም ተደርጎም ሊታይ የሚገባው አይደለም።በኢትዮዽያ ታላላቅ ከተሞች እንደሚስተዋለው ሁሉ ፤ ምዕመናኑ ከመረጠበት ቤተክርስቲያን አባል በመሆን መንፈሳዊ ፍቅርና ሰላም የተመላበትን አገልግሎት ማግኘትና መስጠት መብትና ግዴታው ነው።
ይሁን እንጂ፤ ይህ ቅዱስ አላማ በሶስተኛ ደረጃ በተቛቛመው በቅዱስ ገብር ኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ህይወት ዘርቶ ለማየት አላደለንም።ቤተክርስቲያኑ ከተመሰረተበት ዕለት ጀምሮ ምዕመናኑ ለዕድገቱ መጠናከር ከፍተኛ ጥራት ስናደርግ ነበር። አላማና ግባችን አባላቱ እርስ በርሱ እንዲተዋወቅ፤ ቤተክርስቲያኑ የራሱ ህንፃ እንዲኖረው፤ ከተመሳሳይ ቤተክርስቲያናት ጋር መንፈሳዊ መከባበርና መረዳዳት እንዲኖር ነበር።ነገር ግን በውስጥ የሰፈነው አፍራሽ ሁኔታ ይህን በጎ ባህርይ አላራመደውም። የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ቄስ ያሬድ ገብረመድህን ለዚህ ግብ መሳካት ዝግጁ ሆነው አላገኘናቸውም። ምዕመናኑ ተወያይቶ ያጸደቀውና የተቀበለው መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖረው ከማድረግ ይልቅ ፤በጭፍን ሊያስተዳድሩት ሲጥሩ ይታያሉ። ችግሩ ቤተክርስቲያኑ በኦሃዮ ስቴት ህግና ደንብ ከታክስ ነፃ ሆኖ የተለያዩ ድጋፎችን ለመግኘት ለሚደረገው እንቅስቃሴ እልቅፋት ሆኗል። ንብረትና ገንዘብ ሃላፊነት በጎደለው ባህርይ በዘፈቀደ እዲወጣ ዳርጎታል።ምዕምናኑ በሚያስተባብረው ጉዳይ ከማተኮር ይልቅ በሚለያየው ላይ እንዲጣንከር እየገፋፋው ነው።
የቤተክርስቲያኑ አቅጣጫ ወደተሳሳተ መንገድ መጓዙን የተገነዘቡ አብዛኛው የሰበካ ጉባዔ አባላት እርምት እንዲደረግበት ቢጠይቁም፤ ከአባትነት የሚጠበቅ ምላሽ አላገኙም። ባቀረቡት የሂሳብ ሪፖርት የቤተክርስቲያኑ ወጪ ከገቢው ሊወዳደር አልቻለም በማለታቸው “አጭበርባሪና ዘራፊ” ተብለው ተዘልፈዋል።ለቤተክርስቲያኑ ማሰሪያ እንዲውል በባንክ የተቀመጠን $42ሺ አስተዳዳሪው አውጥተው ወደሌላ አካውንት ለማዛወር ሲጥሩ በባንኩና በሰበካ ጉባዔው አባላት ጥረት ሊከሽፍ እንደበቃም ተጠቁመናል። ይህን የምዕመናኑን ገንዘብ ለማስከበር የጣሩትን አባላት “አላቃቸውም፤ሌቦች ናቸው” ተብለው በኒሁ አስተዳዳሪ ተወንጅለዋል።
ለሁለተኛ ጊዜ ለምዕመናን በታደለውና የቀውሱን መንስዔ በሚገልፀው ሪፖርት እንደተመለከተውም፤ አስተዳዳሪው ቤተክርስቲያኑ “ገለልተኛና የጳጳስ ስም በቅዳሴ እንደማይጥቀስ” ተናግረው ነበር። ይህን ቃላቸውን በመስበር ጳጳስ በመጥራት መቀደስ ተጀመረ። በአብዛኛው ምዕመናን እምነት እርምጃው ጳጳሱንና የሚመሩትን ሲኖዶስ ሽፋን በማድረግ ድብቅ አላማ ለማራመድ የተሤረ እንጂ፤ትክክለኛ አቋም ያለው የሲኖዶስ ምርጫ አይመስለንም። ይህ ቢሆንማ ኖሮ ቤተክርስቲያኑ ከተቋቋመበት ዕለት ጀምሮ በከተማችን ካለው የስላሴ ቤቴክርስቲያን ጋር እጅና ጓንት ሆነን በተጓዝን ነበር።
ባጭሩ፤ ቄስ ያሬድ በአስዳዳሪነትም ሆን በአባትነት ቤተክርስቲያኑን ለመምራት ያላቸው ብቃት ጥያቄ ውስጥ አግብቶናል፤ ሃዘናችንንም ከፍ አድርጎታል።በቤተክርስቲያኑ የሰፈነው ችግር “የእኛ ቤተክርስቲያን ችግር አይደለም” ተብሎ በሁኔታው በመሳለቅ ወይም በዝምታ የሃዘን ስሜት የሚታለፍ እንደማይሆን እምነታችን ፅኑ ነው።የተዛባውን ሁኔታ ለማስተካከል መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ድጋፍ የሚሻ ሆኖ አግኝተነዋል።
ስልዚህም በያላችሁበት በመሆን፤ የቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አስተዳደር ከስህተቱ ተምሮ በተሻለ አስተዳደር አገልግሎቱን እሚቀጥልበት ሁኔታ እንዲመቻች፤ ይህ ሊሳካ ካልቻለ- ምዕመናኑ ወደመረጡበት ነባር ቤተክርስቲያን በፍቅርና በሰላም ተመልሰው ፀሎታቸውን እሚያደርሱበት ወይም በመንፈሳዊ አባትነትቸው ክብርና ፍቅር ባተረፉ አባቶች የሚመራ አዲስ ቅዱስ ገብር ዔል ቤተክርስቲያን ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ማመቻቸት -አስፈልጊ ሆኖ ይታያልና ለዚሁ ድጋፋችሁ እንዳይለይ በአክብሮት እንጠይቃለን።
የፍቅርና የሰላም አምላክ ይርዳን- አሜን

ማሳሰቢያ፤ በሰበካ ጉባዔው አባላት በኩል ለቅዱስ ገብርዔል ምዕመናን የተበተነውን
ሀ/ የሂሳብ ሪፖርት
ለ/ስለተፈጠረው ቀውስ መንስዔ የገለፀውን ሪፖርት እንድታነቡና ላላነበበው እንድታስተላልፉ በአክብሮት እንጠይቃለን
ጉዳዩ ያሳሰባቸው የቤተክርስቲያኑ ምዕመናን፡

Ethiopia Reads founder & Children books author Jane Kurtz speaks in DC area

February 26th, 2008

Come meet Author Jane Kurtz!
Come learn about Ethiopia Reads!


Come hear Jane tell her story of growing up in Ethiopia , how it influenced her writing and the development of the NGO Ethiopia Reads.

[Ethiopia Reads' strive to cultivate love of books among chidren in Ethiopia by building libraries, including the first 'Mobile Donkey library'. http://ebcef.blogspot.com/2006/07/first-donkey-mobile-library-launched.html
Bring your children, they would have memorable fun-time.]

Saturday, March 1, 2008 ~~ 6:00 – 8:00 p.m.
~~ Sidamo Coffee and Tea ~~ 417 H Street NE ~~ Washington , DC 20002~~

There will be a slide show presentation.
Jane’s books Only A Pigeon, the Lion’s Tail (Amharic/English version) and Saba will be available for purchase.
Dual language Amharic/English books ~ The Beekeeper of Lalibela, Fafi’s Sheep and Silly Mammo will be available.
The kitchen at Sidamo will be open for your convenience.

Sunday, March 2, 2008 ~~ 1:30 – 4:00 p.m.
~~Highland Origin Café ~~ 8200 Fenton Street ~~ Silver Spring , Maryland ~~

There will be a slide show and informative session regarding Jane Kurtz and Ethiopia Reads. Additionally, Tsilat Petros will be joining us and sharing her enthusiasm and dreams for Ethiopia and the Ethiopia Reads project. Come hear her story!
The kitchen at Highland Origin Café will be open for your convenience.


Sunday afternoon tune in as Jane Kurtz is interviewed on AM 1390 Zethiopia Radio from 5:00-6:00 p.m.
Jane will be sharing with Dereje Desta the latest news from Ethiopia Reads and will introduce the audience and Ethiopia Reads’ supporters to Tsilat Petros – who will be traveling to Ethiopia to work for Ethiopia Reads!

Monday, March 3, 2008 ~~ 6:00 – 8:00 p.m.
~~ Busboys and Poets ~~ 4251 South Campbell Ave ~~ Arlington , VA 22206 ~~


Come hear Jane tell her story of growing up in Ethiopia , how it influenced her writing and how Ethiopia Reads has developed and she will share the
hope and dreams for Ethiopia Reads’ future.
There will be a slide show presentation.
Light refreshments will be served.
Busboys and Poets have a supply of Jane’s books available for your convenience.


For further information, please contact Catie Dupont.
Catie@EthiopiaReads.org or call 571-243-1411.
An RSVP to any of these events is not necessary, but would be appreciated.
For specific information regarding Ethiopia Reads, please visit ethiopiareads.org

Regards,
Catie Dupont

You gain strength, courage and confidence by every experience in which you really stop to look fear in the face. You must do the thing which you think you cannot do. ~ Eleanor Roosevelt

For Catie Dupont, please e-mail EthiopiaReads@aol.com or Catie@SilverChicks.com. Mobile 571-243-1411.

For additional information regarding Ethiopia Reads, please contact Laura Bond in the Denver office. laura@ethiopiareads.org

Ethiopia - Third Annual Fistula Fundraising Event

December 2nd, 2007

Ethiopia - Third Annual Fistula Fund raising Event

Date: Sunday, Dec. 9,2007
Time: 4:00 p.m. to 7:00 pm
Crystal Gateway Marriott -
1700 Jefferson Davis Hwy -
Crystal City, VA

Click here for more information (PDF)

Ethiopia - STOP THE GROSS HUMAN RIGHTS ABUSES

August 23rd, 2007

Link: http://www.eacamoveon.org

Ethiopian American Civic Advocacy (EACA)

FOR IMMEDIATE RELEASE
Washington, DC August 20, 2007
The Ethiopian American Civic Advocacy (EACA) calls upon the international community to demand for the immediate halt to the atrocious and gross human
rights abuses taking place against Ethiopian civilians in the Ogaden by the Ethiopian authoritarian regime.
The Ethiopian military continues to attack and forcibly displace thousands of civilians in
Ethiopia’s eastern Somali region. The regime’s troops continue to burn homes and property, including the harvest and other food stocks, are confiscating livestock, and in many cases, detain and open fire on, and kill fleeing civilians.
To stop the spreading of humanitarian crisis and the deteriorating region-wide instability, EACA urgently appeals to the international community to pressure the Ethiopian government to act in accordance to the country’s constitution and United Nation treaties
to respect its citizens’ fundamental freedom and rights.
About EACA
The Ethiopian American Civic Advocacy (EACA) is a US based, non-profit, non-partisan community-based civic organization striving to empower Ethiopian-Americans and Ethiopians to fight for the respect of human rights, promote democratic governance, and
demand donor accountability in Ethiopia. For more information about EACA, please contact:
Ethiopian American Civic Advocacy (EACA)
Phone: (703) 665-4042
PO.Box 1292
Lorton, Virginia 22199-1292
USA
http://www.eacamoveon.org
eacadvocacy@gmail.com

Request a Senate Hearing on the Ethiopian Ogaden Crisis: The Ethiopian American Civic Advocacy calls upon the pro-democracy community to demand the immediate halt to the atrocious and gross human rights abuses taking place against civilians in Eastern Ethiopia by the government. The atrocities against poor rural civilians in Eastern Ethiopia
are reaching troubling proportions. Senator Russ Feingold, Chairman of the Senate Subcommittee on African Affairs, has repeatedly expressed his concern about the government atrocities. A senate hearing would initiate policy action on this crisis, and bring much needed attention to Ethiopians' suffering under government abuses. Please
ask Senator Feingold to call for a hearing. ...
Act Now!
http://www.eacamoveon.org/eaca_send_letter.php?letter_id=67